የሀገር ውስጥ ዜና

የሸቤ ሶምቦ ወረዳ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አደረጉ

By Alemayehu Geremew

November 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ዞን የሸቤ ሶምቦ ወረዳ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ የሚውል 50 ሠንጋ እና 600 ኩንታል የምግብ እህል ድጋፍ አደረጉ፡፡

የወረዳው ነዋሪዎች ድጋፉን በቀጣይነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉና ከመከላከያ ሠራዊት ጎን እንደሚቆሙ ነው የገለጹት፡፡

በድጋፍ ፕሮግራሙ ላይ የጅማ ዞን አስተዳዳሪ ቲጃኒ ናስር መገኘታቸውንም ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡