የሀገር ውስጥ ዜና

የአሸባሪው ህወሓት አክቲቪስቶችና ደጋፊ የምዕራባዊያን ሚዲያዎች “ሁመራ ማሳከር” የሚል ሀሰተኛ ዘመቻ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቃቸው ተደርሶበታል

By Feven Bishaw

November 22, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪው ህወሓት አክቲቪስቶችና ደጋፊ የምዕራባዊያን ሚዲያዎች “ሁመራ ማሳከር” የሚል ሀሰተኛ ዘመቻ ከዚህ በፊት እንዳደረጉት ሁሉ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቃቸው ተደርሶበታል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ትናንት ኬንያዊው የደህንነት ጉዳዮች ተንታኝ የኢትዮጵያን እውነት በማዛባትና ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት የሚታወቁት ሚዲያዎች በሱዳን ገዳሪፍ ግዛት መሰባሰባቸውን አጋልጦ ነበር። የኢፕድ ምንጮች የአሸባሪው የጥቅም ተጋሪዎችና ተከፋይ አክቲቪስቶች በሁመራ የጅምላ ጭፍጨፋ ተፈጽሟል በሚል ዘመቻ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።