የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች በሸዋሮቢት ግንባር እየተፋለመ ያለውን ሰራዊት አበረታቱ

By Feven Bishaw

November 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች በሸዋሮቢት ግንባር በአካል በመገኘት አሸባሪዎችን እየተፋለመ ያለውን ሰራዊት አበረታቱ።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከጀግናው የሀገር መከላከያና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት አሸባሪውን ቡድን የሽብር ሴራውን በማክሸፍ በተለያዩ የጦር ግንባሮች በመፋለም ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡