የሀገር ውስጥ ዜና

“የአፍሪካ ቀንድ ተናግሯል” – የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር

By Meseret Awoke

November 22, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ቀንድ ሀቁን ተናግሯል ሲሉ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል በትዊተር ገጻቸው ገለጹ፡፡

ሰሞኑን በቃ ( No More) በሚል ሃሽታግ ኢትዮጵያውያንና የአፍሪካ ቀንድ ዲያስፖራዎች አሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባውያን አገራት ጣለቃ ገብነትን በመቃወም በምልዐት ሰልፍ መውጣታቸው የሚታወቅ ሲሆን÷ አለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፎቹ የአፍሪካዊነት መነሳሳት እና የኩራት ምንጭ መሆናቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን በአንድነትና በፍቅር በአገራቸውና በአህጉራቸው ጣልቃ የሚገቡ አንዳንድ ምዕራባውያንን በማውገዝ ፍላጎቶቻቸውን እና ምኞቶቻቸውን በጋራ ያሳካሉም ነው ያሉት ሚኒስትር የማነ፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!