አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤሊደአር ወረዳ መንግስት ሰራተኞች የአገር መከላከያ ሰራዊትን ለመደገፍ ደመወዛቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ መሆናቸውን ገለጹ።
ሰራተኞቹ ሽብርተኛውን የህወሓት ጁንታ በአገራችን እየፈጸመ ያለውን እኩይ ተግባር ከስሩ ነቅሎ ለመጣል እየተደረገ ባለው ዘመቻ ላይ ለመሳተፍ ፥ ሰራዊቱን መደገፍ በሚቻልበት በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ተወያይተዋል።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ማህሙድ ህወሓት በሌሎች አካባቢወች እየፈጸመ ያለው ውድመትና ጥፋት ሊያመን እና ሊሰማን ይገባል ብለዋል፡፡
እየሞቱና እየተደፈሩ የሚገኙት የእኛው ወገን የሆኑ እናቶች ወንድሞች እህቶቻችን ናቸው ያሉት አስተዳዳሪ፥ የቡድኑ ጥፋት ካልደረሰብን ብለን እጃችንን አጣጥፈን የምንቀመጥበት ወቅት አለመሆኑን አስረድተዋል፡፡
ወራሪውን ሀይል ከአገራችን ከስሩ ነቅሎ ለመጣል በሚደረገው ዘመቻ ላይ የመንግስት ሰራተኛው የበኩሉን ድጋፍና አስተዋጽኦ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ሰራተኞቹ በበኩላቸው ፥ አገርን ከወራሪ ሀይል ለመታደግ በሚደረገው ዘመቻ ላይ የሚችሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ እና ከአንድ ወር ደመወዛቸው 15 በመቶ ተቀንሶ ለመከላከያ ድጋፍ እንዲሰጥ በሙሉ ድምጽ ተስማምተዋል፡፡
ህዝቡ በሚነዙ አሉባልታወች ሳይሸበር አካባቢውን ተደራጅቶ ነቅቶ መጠበቅ እንደሚገባውም በመድረኩ ተነስቷል።
በአሊ ሹምባህሪ
አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!