አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሃት የሽብር ቡድን በአዲስ አበባ እና በዙሪያው ለሽብር ተግባር ያሰማራቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።
በከተሞች በህብረተሰቡ ውስጥ በተለያዩ መንገዶች በመመሳሰል እንዲገቡ በማድረግ አዲስ አበባ እና በዙሪያው ተልእኮ ሰጥቶ በማስገባት ለሽብር ተግባር እየተንቀሳቀሱ መሆኑን እንደተደረሰበት የፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ ገልጸዋል።