አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት 13 ሺህ 806 ብርድ ልብስ እና 5 ሺህ አንሶላ ለመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ድጋፍ አድርጓል፡፡
በድጋፉ ወቅት የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሃብት አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ ኮሎኔል ተመስገን አስማማው÷ ድጋፍ ያደረግነው ሁሌ ከሰራዊታችን ጎን መሆናችንን ለማሰያት ነው ብለዋል ፡፡