የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት አጋርነታቸውን ማጠናከር በሚችሉባቸው አግባቦች ዙሪያ ተወያዩ

By Meseret Awoke

November 24, 2021

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ከአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢታ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸው ወቅት በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት መካከል ባለው ትብብር ዙሪያ መክረዋል።

ከዚህ ባለፈም በመካከላቸው ያለውን የረጅም ጊዜ አጋርነት ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ መወያየታቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም ጠንካራ ትብብር መዘርጋት በሚቻልበት አግባብ ላይ ምክክር አድርገዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!