የሀገር ውስጥ ዜና

ሰራዊቱ በሕዳሴ ግድብ ቀጠና አስተማማኝ ሰላም በማስፈን ግዳጁን እየተወጣ ነው

By Meseret Awoke

November 24, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቀጠና አስተማማኝ ሰላም በማስፈን በጀግንነት ግዳጁን እየተወጣ እንደሆነ ተጠቆመ፡፡

ከጀግናው የአገር የመከላከያ ሰራዊታችን ጎን ተሰልፈው ግዳጅ በመፈፀም ላይ የሚገኙ የፌዴራል ፖሊስ ፣ የአማራ ፣ የጋምቤላ ፣ የሲዳማ ፣ የደቡብ ክልል እና የቤኒንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታ አካላትም አገራዊ ተልኳዕቸውን በጀግንነት በመፈፀም ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ አሻራ ያረፈበት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያለአንዳች የፀጥታ ችግር ግንባታው እተከናወነ ሲሆን፥ ሰራዊቱ በቀጠናው ቀን ከሌት ግዳጁን በማከናወን ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ጠላት ቀጠናውን ለማተራመስ በቅጥረኛ ተላላኪ ሃይሎች አማካኝነት በተደጋጋሚ ትንኮሳ ቢሞክርም በሕዳሴው ዘቦች አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ሽንፈት መከናነቡን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአሁኑ ሰአት በቀጠናው የተሰማሩ የሰራዊታችን ክፍሎች ፣ የሜካናይዝድ እና አግረኛ ክፍለጦሮች ፣ የክልል የልዩ ሃይል አባላት በተጠንቀቅ ሆነው ግዳጃቸውን በመፈፀም ላይ ይገኛሉ፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!