የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያና እስራኤል በኢንቨስትመንት የድጋፍ ስራዎችን በጋራ መስራት በሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያዩ

By Feven Bishaw

November 24, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜና ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይቱ የሁለቱን አገራት የቆየ የኢንቨስትመንት ግንኙነት አጠናክሮ ስለመቀጠል፣ በጋራ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አማራጮች ለእስራኤል ባለሀብቶች ማስተዋወቅ በሚቻልበት አግባብ ላይ መክረዋል።