አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራባውያንን ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰልፍ አዲስ አበባ በሚገኘው እንግሊዝ ኤምባሲ ፊት ለፊት እየተካሄደ ነው።
የሰልፉ ታዳሚዎች በአዲስ አበባ የእንግሊዝ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት ለኢትዮጵያ የውጪ ጣልቃገብነትን የሚቃወም ደብዳቤ ለእንግሊዝ ኤምባሲ አስገብቷል።
ሰልፈኞቹም የምዕራባውያን ሚዲያዎች ከሚያሰራጩት ሃሰተኛ ፕሮፓጋንድ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
ከዚህ ባለፈም ምዕራባውያን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ከሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት እንዲቆጠቡም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!