የሀገር ውስጥ ዜና

ዶክተር ሊያ ታደሰ አገልግሎት ሲሰጡ ለቆዩ የቻይና የህክምና ቡድን አባላት ምስጋና አቀረቡ

By Meseret Awoke

November 25, 2021

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ላለፈው አንድ አመት በጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል የህክምና አገልግልት ሲሰጡ ለቆዩ የቻይና የህክምና ቡድን አባላት ምስጋና አቀረቡ።

ሚኒስትሯ የቻይና መንግስት የኢትዮጵያን የጤና ስርአት ለማጠናከር ለሚያደርገው ጥረትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የህክምና ቡድን አባላቱ ላለፈው አንድ አመት በጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት በመስጠት እና የእውቀት ሽግግር በማድረግ ቆይተዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!