አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአፋር ሕዝብ ጠላትን የሽንፈት ካባ አከናንቦ መመለስ ጥንትም የነበረ አኩሪ የጀግንነት ባሕሉ ነው ሲሉ የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ሙሳ አደም ገለጹ፡፡
አሸባሪው የህወሓት ቡድን ሰርጎ በገባባቸውና ወረራ በፈጸመባቸው የአፋር አካባቢዎች የፀጥታ መዋቅሩና ሕዝቡ ባደረጉት የተቀናጀ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ሠብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበት ወደ መጣበት ተመልሷል።