አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገር መከላከያ ሠራዊት እየፈጸመ ባለው ጀብዱ ኩራት እንደተሰማቸው እና ሠራዊቱን ለመቀላቀል ፍላጎት እንዳደረባቸው የፍኖተ ሰላም ከተማ ወጣቶች ተናገሩ፡፡
የአገር መከላከያ ሠራዊት ለነጻነት እና ለአገራዊ ክብር ሲል ጀብዱ እየፈጸመ መሆኑን የገለጹት ወጣቶች እነሱን ጨምሮ ሁሉም ወጣት በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ በመግባት አገርን ከመፍረስ ለማዳን በሚደረገው የሕልውና ዘመቻ በመሳተፍ የታሪኩ አንድ አካል መሆን እንደሚፈልጉ ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡