አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎፋ ዞን “እኔም የዘማች ቤተሰብ አካል ነኝ’ በሚል መሪ ቃል ለዘማች ቤተሰብ ድጋፍና ለሠራዊቱ የደም ልገሳ እየተደረገ ይገኛል።
በዞኑ ሱካ ቀበሌ ይፋዊ የዘማች ቤተሰብ ድጋፍ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን ÷ በመርሃ ግብሩ የደቡብ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ማሄ ቦዳ እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ሃላፊው በዚህ ወቅት እንደገለጹት ÷ ከውስጥም ከውጭ የተገዙ ባንዳዎች በተደጋጋሚ ጦርነት ቢከፍቱብንም ለአንድም ጊዜ ሳትሸነፍ ጠላትን አሳፍራ ክብሯን አስጠብቃ የኖረች ኢትዮጵያ ዛሬም ጦርነቱን በድል ታጠናቅቃለች ማለታቸውን ደሬቴድ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!