የሀገር ውስጥ ዜና

በአሸባሪው ቡድን ወረራ በአማራና በአፋር ለተፈናቀሉ ከ1 ሚሊየን 76 ሺህ በላይ ዜጎች ድጋፍ እየተደረገ ነው – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አግልግሎት

By Meseret Awoke

November 27, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ቡድን ወረራ በአማራና በአፋር ለተፈናቀሉ ከ1 ሚሊየን 76 ሺህ በላይ ዜጎች የመሰረታዊ ሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አግልግሎት ገለጸ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አግልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ዛሬ ረፋድ በሰጡት መግለጫ ፥ በአማራ ክልል በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ጥቃትና ወረራ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን በላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ለእነዚህ ዜጎች መሰረታዊ የምግብ አቅርቦት ለማድረስ ባለፉት ሦስት ቀናት ብቻ ወደ 265 ሺህ 291 ኩንታል ምግብ በተለያሰየ መልኩ እንዲሰራጭ ተደርጓል።

በዚህም ከ1 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ለማደገፍ ተችሏል ነው ያሉት።

በአፋር ክልል እንዲሁ በወራሪው ቡድን ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉት ዜጎች ቁጥር አሁን ላይ 76 ሺህ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ካለፈው ወር ወዲህ ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ36 ሺህ ኩንታል በላይ መሰረታዊ የምግብ አቅርቦት ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በወራሪው ቡድን ጥቃት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሚደረገው መሰረታዊ ድጋፍ በዋነኛነት በመንግሥት እና በአጋር ድርጅቶች አማካይነት እንደሆነም ነው ሚኒስትር ዴኤታዋ የገለጹት።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!