የሀገር ውስጥ ዜና

ጠመንጃ ያዥ አካባቢ የተለያዩ መሣሪያዎች ትቦ ዉስጥ ተጥለው ተገኙ

By Meseret Awoke

November 27, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ልዩ ቦታዉ ጠመንጃ ያዥ አካባቢ የተለያዩ መሣሪያዎች ትቦ ዉስጥ ተጥለው ተገኝተዋል።

ፖሊስ ኅብረተሰቡ አካባቢውን በንቃት እንዲቃኝና የተለየ ነገር ሲመለከት ለፖሊስ እንዲያመለክት አሳስቧል።

በዚህም ፡-

1) ታጣፊ ከላሽ ብዛት 1 የውግ ቁጥር 24096 የጥይት ብዛት 114 እና 4 ካዝና

2) ማካሮፍ ሽጉጥ ብዛት 1 የውግ ቁጥሩ የማይታይ የጥይት ብዛት 7 ፍሬ

3) አንድ የአፋር ግሌ የሚመስል ሳንጃ ሲሆን በቀን 17/03/2014 ዓ/ም ተይዞ ለፖሊስ ጣቢያ ገቢ ሆኗል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!