የሀገር ውስጥ ዜና

በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ከጥቂት ቀናት በፊት እንደገና ተጀምሯል

By Meseret Awoke

November 27, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ከጥቂት ቀናት በፊት እንደገና መጀመሩን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በመግለጫው አስታውቋል፡፡

ድጋፉን የሚያደርገው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወደ ክልሉ የሚያደርገውን የሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ አውሮፕላኖች በረራዎች መደረጋቸውን መግለጫውን የሰጡት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ገልጸዋል፡፡

አክለውም ÷ በሰመራ በኩል አስፈላጊውን ሂደት ያለፉ 83 ድጋፍ የያዙ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ መላካቸውን ሚኒስትር ዴኤታዋ አንስተዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!