Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የህንዱ ግዙፍ የመድኃኒት አምራች ድርጅት በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ጉብኝት አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንዱ ግዙፍ መድኃኒት አምራች ዙቪየስ ላይፍሳይንስ የመድኃኒት አምራች ድርጅት ስራ አስኪያጅ የተመራ ልዑክ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ፡፡
ውይይታቸውም÷ በቀጣይ የኢንቨስትመንት ቅደም ተከተላቸው እና እቅዶቻቸው ላይ ያተኮረ መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከውይይታቸው በኋለም የልኡካን ቡድኑ የቂሊንጦ ኢንደስትሪ ፓርክን ጎብኝቷል፡፡
የልዑካን ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቱ በፊት÷ በበይነ መረብ ከኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ፣ ከምክትል ኮሚሽነር ዳንኤል ተሬሳ እንዲሁም ከአምባሳደር ደሚቱ ሃምቢሳ ጋር በኢትዮጵያ የፋርማሱቲካል ሴክተር ኢንቨስት ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ይታወሳል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version