አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ1ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው መድኃኒቶች ከውጭ ተገዝተው ወደ አገልግሎት ተቋሙ መግባታቸውን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡
በኤጀንሲው የመድኃኒትና የህክምና መገልገያዎች የግዥ ኮንትራት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ናሆም ገመቹ እንደገለጹት÷መድሃኒቶቹ ካሳለፍነው ወር መጨረሻ ጀምሮ ነው ወደ ተቋሙ መጋዘኖች የገቡት፡፡
ከእነዚህ መድኃኒቶች ውስጥም 1 ቢሊየን 77ሚሊየን 555 ሺህ 528 ብር ዋጋ ያላቸው የህይወት አድን መድኃኒቶች፣ 161 ሚሊየን 493 ሺህ 906 ብር ዋጋ ያላቸው መሰረታዊ መድኃኒቶች እና 2 ሚሊየን 421ሺህ 552 ብር ዋጋ ያላቸው የህክምና መሳሪያዎች ይገኙበታል፡፡
መድኃኒቶቹ 1ቢሊየን 241 ሚሊየን 470 ሺህ 987 ብር ወጪ የተደረገባቸው መሆኑን ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
መድኃኒቶቹ የህብረተሰቡን የመድኃኒት ፍላጎት ለማሟላት እንደሚያግዙም ተመላክቷል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!