Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለህዳሴ ግድብ በድረገጽ ከ 270 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 20 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በድረ ገጽ ከ 270 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ ተሰበሰበ፡፡
ድጋፉ የተሰበሰበው ሐምሌ 18 ቀን 2013 ዓ.ም ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ድረ ገፅን መሰረት በማድረግ የተዘጋጀውን ፕላትፎርም www.mygerd.com በመጠቀም ነው፡፡
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ባሉት አራት ወራት ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ርብርብ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡
በትልቅ ዓለም አቀፋዊ ጫና ውስጥ የታየው ርብርብ ከፍተኛ የትብብርና የአንድነት ስሜት የታየበት ነውም ተብሏል፡፡
እስከዛሬ ድረስ 1855 ለጋሾች ተሳትፈውበት 270 ሺህ 952 የአሜሪካ ዶላር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማሰባሰብ ተችሏል መባሉን ከኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ድጋፉ ከተለያዩ ተቋማት እና ግለሰቦች የተሰበሰበ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version