አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሶስተኛ ጊዜ በአፍሪካ ቀንድ የሚገኙ አርብቶ አደሮችን ስርአተ ምግብ ለማሻሻል ያለመ የፓናል ውይይት በጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በዛሬው እለት ተካሂዷል፡፡
በፓናል ውይይቱ ዓለም አቀፍና አገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅቶችን ጨምሮ በሶማሌ ክልል የሚገኙ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተሳተፉ ሲሆን፥ ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ ተመላክቷል ።
የጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማሩ በተጨማሪ ጥናት እና ምርምሮችን በማካሄድ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት የተለያዩ ስራዎችን እንደሚሰራም ተገልጿል ።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር በሽር አብዱላሂ፥ በክልሉ በተደጋጋሚ በሚከሰተው ድርቅ ምክንያት በእናቶች እና ህፃናት ላይ በሚከሰተው የስርአተ ምግብ መዛባት ችግርን ለመቅረፍ በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ መግለፃቸውን የሶማሌ ክልል ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

