Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሀይሌ ሪዞርት ሠራተኞች ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ለሀገሬ እኔም ሀይሌ ነኝ” በሚል መሪ ሃሳብ የሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ሰራተኞች ለአገር መከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳና የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ።
አገር ሰላም ካልሆነች ሰርቶ ማግኘት አይቻልም ያሉት የሪዞርቱ ሰራተኞች፥ “ለአገሬ እኔም ሀይሌ ነኝ” በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ ለሰራዊቱ 66 ዩኒት ደም ከመለገስ በተጨማሪ የ300 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።
የሪዞርቱ ስራ አስኪያጅ አቶ እምሻው ተሾመ ድጋፉን ለደቡብዝ ጠቅላይ መምሪያ ሲያስረክቡ እንዳሉት መከላከያ ሰራዊቱ አገር ለማኖር ህይወት እየሰጠ እኛ ትንሿን የምትተካ ደምና ገንዘብ መስጠታችን ትልቅ ነገር አይደለም።
መኖርም ሰርቶ ማግኘትም የሚቻለው አገር ስትኖር ነው ያሉት አቶ እምሻው ጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት አገር ለማዳን የሚያደርገውን ተጋድሎ ማገዝ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው ብለዋል።
285 የሪዞርቱ ሰራተኞች 300 ሺህ ብር አዋጥተን ለጀግናው የአገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አድርገናል ነው ያሉት።
የሪዞርቱ ሰራተኞች ዛሬ ለ14ኛ ጊዜ ባደረጉት የደም ልገሳ 66 ዩኒት ደም መለገሳቸውን ገልጸው፥ የህልውና ዘመቻውን ለመቀላቀል ዝግጁ ናቸው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ኮሎኔል ተሻለ ቱማ ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት የሰራዊቱን ተጋድሎ ለማገዝ መላው ኢትዮጵያዊ እያደረገ ያለው ርብርብ ለሰራዊቱ የሞራል ስንቅ መሆኑን ገልጸዋል።
የሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ሰራተኞች ልክ እንደ ሻለቃ ሀይሌ ሰራዊቱን በማገዝ ያበረከታችሁት የገንዘብና የደም ልገሳው ሰራዊቱ ድል እንዲቀዳጅ ብርታት ይሆነዋልም ነው ያሉት።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version