Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለሠራዊቱ አጋርነታችንን ማሳየት ግዴታችን ነው – የሠመራና ሎግያ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከጠላት ጋር በጀግንነት በመፋለም ህይወቱን እየገበረ እኛ ደግሞ ወገናዊ አጋርነታችንን በተግባር ማሳየት ግዴታችን ነው አሉ በአፋር ክልል የሠመራና ሎግያ ከተማ ነዋሪዎች።
በከተማዋ የሚኖሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለዘማች ቤተሰቦች የቁሳቁስ ድጋፍና በዱብቲ ሆስፒታል ህክምና ላይ ለሚገኙ የሠራዊቱ አባላት የምሳ ግብዣ አድርገዋል።
ነዋሪዎቹ፥ ከከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ከህብረተሰቡ ባሰባሰቡት ገንዘብ ምግብ አዘጋጅተው ምሳ በመጋበዝ ከጀግኖቹ ጋር አብረው ማሳለፍ በመቻላቸው ደስተኛ እንደሆኑ ይናገራሉ።
እንዲሁም ለዘማች ቤተሰቦች በነፍስ ወከፍ ከተደረገው የአስቤዛ ድጋፍ ውስጥ 10 ኪሎ ግራም ዱቄት ፣ አንድ ሊትር የምግብ ዘይት፣ አንድ ኪሎ ግራም ሽሮ፣ በርበሬና ስኳር እንደሚገኙባቸው ተገልጿል።
ህብረተሰቡን በማስተባበር እየተደረገ ያለው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነዋሪዎቹ አረጋግጠዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version