አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በ8ኛው የቻይና አፍሪካ የትብብር የሚኒስትሮች ፎረም ላይ ተሳተፈች።
በሴኔጋል ዳካር በተካሄደው ፎረም ላይ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የተመራ ልዑክ ተሳትፏል።
በፎረሙ መክፈቻ ላይ የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ በቀጣዮቹ አመታት በአፍሪካ የሚተገበሩ ፕሮጀክቶችንይፋ አድርገዋል።
ፕሮጀክቶቹ የጤናውን ዘርፍ ጨምሮ፥ በድህነት ቅነሳ፣ ንግድ፣ የኢንቨስትመንት ማስተዋወቂያ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በአቅም ግንባታ ፕሮግራሞች ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ከዚህ ባለፈም የባህል እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲሁም ሰላምና የፀጥታ ጉዳዮችን ያካተቱ መሆናቸው ተመላክቷል።
ፕሬዚዳንት ዢ ቻይና በተለያዩ መስኮች የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የሚሰጠውን የሉባ ሰርቶ ማሳያ ማዕከልን ለማቋቋም እና የቻይና ኩባንያዎችን ለማበረታታት ከአፍሪካ አገራት በትብብር መስራቷን ትቀጥላለች ብለዋል።
የሉባ ፕሮጀክት በአፍሪካ በጥቂቱ 800 ሺህ የስራ እድሎችን ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

