Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የደብረ ብርሃን ከተማ መምህራን እና ሠራተኞች የዘማች ቤተሰቦችን ሠብል ሰበሰቡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረ ብርሀን ከተማ የሚገኘው የኃይለ ማርያም ማሞ መሰናዶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንና ሠራተኞች የዘማች ቤተሰቦችን ሠብል ሰበሰቡ።

ሠብል ሲሰበስቡ ያገኘናቸው መምህራን እንዳሉት ÷ የትግራይ ወራሪ ኃይልን ለመፋለም በግንባር የሚገኙ ወገኖችን ሠብል በመሰብሰብ አጋርነታችንን እንገልጻለን ብለዋል።

ሠብላቸው የተሰበሰበላቸው ወ/ሮ በሰልፌ ይፍሩ እና ሻምበልባሻ ፍቅረ እሸቴ ÷ ስራውን ያከናዉኑላቸው የነበሩ ልጆቻቸው በግንባር በመገኘታቸው በእርሻ ሥራ ላይ ክፍተት ይፈጠራል ብለው ቢሰጉም ሠብላቸውን መምህራኑ በመሰብሰባቸው ክፍተት እንዳልተፈጠረ ገልጸው መምህራኑ ላደረጉላቸው አጋርነት አመስግነዋል።

የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ንጉስ ደስታ በበኩላቸው ÷የት/ቤቱ መምህራንና ሠራተኞች ለህልውና ዘመቻው አጋርነታቸውን ለመግለጽ ሠብል ከመሰብሰብ ባሻገር ከ57 ሺ ብር በላይ በማሰባሰብ በግንባር ለሚገኘው ሠራዊት ስንቅ ለማዘጋጀትም እየተንቀሳቀሱ ነው ብለዋል።

ለዘማች ቤተሰብ የሠብል አሰባሰብ ሥራው እንደሚቀጥልም ርዕሰ መምህሩ ተናግረዋል።

በግርማ ነሲቡ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version