አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “የምእራባውያን ጫና እና የምሁራን ሚና” በሚል ሃሳብ በመዲናዋ የውይይት መድረክ የተካሄደ ሲሆን÷ ኢትዮጵያን የሚያቆም እና የሚያስቀጥል ተግባር ተባብረን እንስራ ሲሉ ምሁራን ጥሪ አቀረቡ፡፡
በውይይቱ እየተሳተፉ የሚገኙ ምሁራን የውጭ ሀይላት የሚያድርጉትን ጣልቃ ገብነት ለመከላከል ያለንን እውቀትና ልምድ ሀገርን ለሚጠቅም አላማ በማዋል መታደግ አለብን ብለዋል::
በአለም አቀፍ ሚዲያዎችና ጆርናሎች ላይ ከመፃፍ ጀምሮ ያሉ አጋጣሚዎችን በመጠቀም የሀገርን እውነታ ማጉላት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በተለያዩ የውጭ ሚዲያዎች ኢትዮጵያን በሚመለከት እየወጣ ያለው ዘገባ መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር ተቃራኒ መሆኑን ለአለም ማህብረሰብ ማሳወቅም ይጠበቃል ነው ያሉት ምሁራኑ::
“ያልከፈልነው የሀገር ውለታ አለብን” ስለሆነም ይህን መሰረቱ ያደረገ ግንባር መፍጠርና ለተጀመረው ትግል ባለን አቅም ደጀን ለመሆን እንጣርም ሲሉ ነው የተናገሩት::
አሁናዊው የሀገራት ጫና ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን ከአሸባሪው ቡድን ፅንሰት ጋር የሚገናኝ እንደሆነ ያነሱት ምሁራኑ÷ አላማውም አሻንጉሊት የሆነን እካል በስልጣን ላይ ማስቀመጥ እና ድብቅ የሆነውን ሴራቸውን ማራመድ ነው ብለዋል፡፡
አንዳንድ ምዕራባውያን ያለ የሌለ አቅማቸውን በመጠቀም ሀገር የማፍረስ ሴራቸውን በባንዳዎች ድጋፍ ቀጥለውበታልም ነው የተባለው::
በአሸብር ካሳሁን
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

