አዲስ አበባ ፣ ህዳር 22፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ ጉብኝት ቤጂንግ ለኢትዮጵያ መንግስት ያላትን አጋርነትና የጠበቀ ወዳጅነት ዳግም በተግባር ያረጋገጠችበት ነው ሲሉ ምሁራን ተናገሩ፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ የዲፕሎማሲና የህግ ምሁራን፥ ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ ከተነሱ ሀይሎች ጎን ለቆሙ የምዕራቡ ዓለም መንግስታት ጠንካራ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው ብለዋል።
በተለይም አዲስ አበባን የዲፕሎማሲ ማዕከልነት በማጥላላት ሀሰተኛ ዘገባ ሲሰሩ ለከረሙት ሚዲያዎቻቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መምጣት ሴራቸውን ያጋለጠ መሆኑን ተናግረዋል ።
የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ጥናትና ምርምሮችን የሰሩት እና ደራሲ አቶ አስናቀው ሲሳይ፥ በአገራት የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ከማድረግ የምትቆጠበው ቻይና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማክበር የምታደርገውን ጥረት መደገፏን ስትገልጽ የነበረውን አቋሟን በተግባር የገለጠ ጉብኝት ብለውታል፡፡
ይፋዊ ጉብኝቱ የአፍሪካ የልማት ሞዴል ለሆነችው ኢትዮጵያ ጫናዎችን እንድታቋቁም ብርታት የሚሰጥ ፤ በሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ ተጽእኖ ሊያንበረክኳት ለሚሹ ሀፍረትን የሚያከናንብ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህሩና የአገሪቱን ፖለቲካ በቅርብ የሚተነትኑት አቶ ስሜነህ ኪሮስ፥ ቻይና በወሳኝ ወቅት ከጎናችን መሆኗ ለእነ አሜሪካ አካሄድ መልስ የሚሰጥ ነው ብለዋል ።
ምሁራኑ ቻይና ዳግም ከኢትዮጵያ ጎን መቆሟን በቃል ሳይሆን በተግባር ያሳየችበት ሁነት ብለውታል፡፡
በሀይለየሱስ መኮንን
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

