አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ያለው ጦርነት ከተጠናቀቀ በኋላ ፈረንሳይ የጀመረችዉን የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት እድሳት ፕሮጀክት እንደምታስቀጥል በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማርቹዌክ አስታውቀዋል፡፡
አምባሳደሩ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ጋር ባደረጉት ዉይይት÷ ፈረንሳይ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገር መሆኗን ገልፀዋል፡፡
በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ጦርነት ከተጠናቀቀ በኋላ÷ ፈረንሳይ የጀመረችዉን የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት እድሳት ፕሮጀክት እንደምታስቀጥል መግለጻቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር በለጠ ሞላ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ላሊበላ ከሽብር ቡድኑ ወረራ ነፃ ስለወጣች የተፈናቀሉ የከተማዋ ዜጎች ከተቋቋሙ በኋላ ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ እንደሚጀምር ያላቸውን እምነት አምባሳደሩ ተናግረዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

