አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኤድና ሞል በሚገኘው የአቶ ተክለብርሃን አምባዬ ቢሮ ውስጥ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ስም የተጻፈባቸው፣ ከብር የተሠሩና ከቤተ መንግሥት የጠፉ ቅርሶች ፖሊስ ባደረገው ብርበራ ተገኙ።
በብርበራው ከቤተ መንግስት ከተሰረቁት ቅርሶች ጋርም የመገናኛ ሬዲዮዎችና የጦር መሣሪያዎችም ተይዘዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ከሽብርተኛው ህወሃት ጋር ግንኙነት ያላቸውንና ሌሎች ህገወጦችን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል እየተወሰደ ባለው እርምጃ አሁንም በርካታ ህገወጥ መሳሪያዎችና የተለያዩ ሰነዶች በፖሊስ እየተያዙ ይገኛሉ፡፡