Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የደርሳ ጊታ ነዋሪዎች አሸባሪው ህወሓት ወረራ ፈፅሞ በቆየባቸው ቀናት ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል አደአር ወረዳ የደርሳ ጊታ ነዋሪዎች የሽብር ቡድን የሆነው ህወሓት ወረራ በፈፀመባቸው ቀናት በሰው እና በንብረታቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት እና ውድመት ማድረሱን ተናገሩ፡፡
በአፋር ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ህወሓት ሾልኮ በመግባት ወረራ በፈፀመባቸው ቦታዎች በሰው ህይወት ላይ፣ በተለያዩ የመሰረተ ልማት ተቋማት እና በግለሰብ ንብረቶች እንዲሁም በሀይማኖት ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እና ውድመት ማድረሱ ተገልጿል፡፡
በደርሳ ጊታም በተመሳሳይ አሸባሪው ህወሓት በሰው ህይወት ላይ ካደረሰው ጉዳት በተጨማሪ በተለያዩ ተቋማት እና የግለሰብ ንብረት ላይ ስርቆት እና ከፍተኛ ውድመት ፈፅሟል ።
ጉዳት የደረሰባቸው የአካባቢው ነዋሪዎችም÷ አሸባሪው ህወሓት ያደረሰብን ጉዳት የሰው ልጅ ይፈፅመዋል ተብሎ የማይገመት እጅግ አሰቃቂ ነው ብለዋል።
በዚህም ማዘናቸውን ገልፀው ÷ በወገን ጦር ታላቅ ተጋድሎ እና መስዋዕትነት ድል አድርገው ደርሳ ጊታን በመቆጣጠራቸው ደስታ እንደተሰማቸው መግለፃቸውን ከአፋር ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

Exit mobile version