Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትራችን ወደ ግንባር በዘመቱበት ወቅት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትራችን ወደ ግንባር በዘመቱበት ወቅት እኛ ደግሞ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየሰራን ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ፡፡
በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራ የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ዙሪያ በኦሮሚያ ልዩ ዞን በአቃቂ ወረዳ በመስኖ እየለማ ያለውን የስንዴ ማሳ ጎብኝቷል፡፡
በዘንድሮው መስኖ ልማት በኦሮሚያ ክልል እስካሁን 180 ሺህ ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑ ተገልጿል፡፡
በ2013/14 የምርት ዘመን በክልሉ በግብርና ዘርፍ በተሰራ ስራ ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በአገር ውስጥ መተካት ተችሏል ነው የተባለው፡፡
የአርሶ አደሩን የውሃ ፓምፕ ፍላጎት ለማሟላትም እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የኦሮሚያ ክልል መንግስትም ፓምፖቹን ከውጭ ለማስገባት በትኩረት እየሰራ ነው ማለታቸውን ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version