Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

መንግስት የህፃናት መቀንጨርን ለማስወገድ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰቆጣ ቃልኪዳን የማስፋፊያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረና በኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የተመራ የውይይት መድረክ በበይነ መረብ አማካይነት ተካሂዷል።
“በቶኪዮ የሥነ ምግብ ዕድገት 2021 የመሪዎች የጎን ለጎን ጉባኤ” በሰቆጣ ቃልኪዳን ፕሮግራም ዙሪያ ነው የበይነ መረብ ውይይት የተካሄደው።
በውይይቱ የኢትዮጵያ መንግስት የህፃናት መቀንጨርን ለማስወገድ በምግብ እና ሥርዓተ ምግብ ላይ ትኩረት በማድረግ ሲሰራ እንደቆየና እየሰራ መሆኑን ዶክተር ሊያ አስረድተዋል።
ለፕሮግራሙ ትግበራም የባለድርሻ አካላትን አስተዋፅኦ ማጠናከር እና ስኬቶችን ማስፋት እንደሚገባ ገልፀው፥ የየሀገር ውስጥ የፋይናንስ አቅምን እና የባለድርሻ አካላት አስተዋፅኦ በማሳደግ የኢኖቬሽን ምዕራፍ ትግበራን ለማስተግበር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሰቆጣ ቃል ኪዳን ትግበራን ለማፋጠን እና የዘላቂ ልማት ግቦችን አጀንዳ ለማሳካት በተደረገው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የተለያዩ አገራት ሚኒስትሮች፣ የአለም አቀፍ አጋር ድርጅት አመራሮች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት አካላት መሳተፋቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የሰቆጣ ቃል ኪዳን ስምምነት ፕሮግራም በመቀንጨር የተጠቁ 6 ሚሊየን ህፃናትን ለመታደግ የሚያስችል እንደሆነ በወቅቱ ተገልጿል።
የሰቆጣ ቃል ኪዳን ፕሮግራም የሙከራ ምዕራፍ ትግበራ በ2012 ዓ.ም ሲጀመር ፕሮግራሙን ለማሳካት በተያዘው 477 ሚሊየን ብር በጀት፥ በፍጥነት ለውጥ በሚያመጡ የግብርና፣ የትምህርት፣ የእናቶችና ህጻናት ጤና አጠባበቅ፣ በውሃ አቅርቦት፣ በመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታና ሌሎች ልማቶች ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራም መገለጹ ይታወቃል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version