አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽነሮች አስቸኳይ ልዩ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።
ጉባኤው ‘ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት’ በሚል መሪ ሀሳብ ነዉ እየተካሄደ የሚገኘው።
በጉባኤው ላይ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤልና ሌሎች የኮሚሽኑ አመራሮች እንዲሁም የክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ተገኝተዋል።
በጉባኤው ላይ መንግስት እየወሰደ ያለዉ የሕልውና ማስከበር ዘመቻ የተገኙ ድሎች፣አፈጻጸምና በቀጣይ ዘመቻውን ወደላቀ ደረጃ ማድረስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ዉይይት ይደረጋል።
የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮቹ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሮች በወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የጸጥታ አካላት የግዳጅ አፈጻጸም አስመልክቶ በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ ውይይት ያደርጋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

