አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ሽብርተኛውን ህወሃት ማዉገዛቸዉ የሚበረታታ እና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ÷በኢትዮጵያ ሉአላዊነት እና ክብር ላይ ፈፅሞ እንደማይደራደሩ ድምፃቸውን ያሰሙት ነዋሪዎቹ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ እየሰራ ላለው ጠንካራ ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ ስራ ያላቸውን አጋርነት ገልፀዋል ብለዋል ።
ሰልፈኞቹ በአደባባይ በነቂስ በመዉጣትም ይህንን ፀረ ኢትዮጵያ የሆነ ቡድን ማዉገዛቸዉ የሚበረታታ እና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው ሲሉ አስፍረዋል፡፡
የትግራይ ተወላጆች ከሌሎች እህት ወንድማቸው ከሆነዉ የአዲስ አበባ ነዋሪ ጋር በመሆን በከተማው ዘርፈ ብዙ የሰላምና ፀጥታ ማስከበር ፣ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የብልፅግና ስራዎች ላይም በንቃት መሳተፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አስተላልፋዋል።
በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች አሸባሪውን ህወሃት በማውገዝ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!