አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የጎተራ ፑሽኪን፣ የቦሌ ሚካኤል ቡልቡላ እና የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጎሮ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ያሉበትን የግንባታ ደረጃ ጎበኙ፡፡
ከንቲባዋ በጉብኝታቸው የመንገድ ግንባታዎቹ ያሉበትን ደረጃ ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን፥ በግንባታቸው ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮች በትኩረት ተፈተው ግንባታቸው በፍጥነት ተጠናቆ ለህዝብ አገልግሎት እንዲውል አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ “እየተከናወነ ያለው ፍሬያማ የፕሮጀክት አፈፃፀም “ኢትዮጵያን እናንበረክካለን” ብለው በየሄዱበት ሁሉ የህዝብ አንጡራ ሀብቶችን እያወደሙ ላሉት አሸባሪ ቡድኖች ኢትዮጵያን ማንበርከክ እንደማይቻል ከማሳየቱም በላይ፣ በየግንባሩ እየደረሰበት ካለው ሽንፈት ያልተናነሰ ተጨማሪ ሽንፈት በመሆኑ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል” ብለዋል።
በከፍተኛ ወኔና የአገር ፍቅር በግንባታ ስራው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ የግንባታ ሰራተኞች፣ አመራሮችና ተቋራጮች ሌትና ቀን መስራት በመቻላቸው ትልቅ ክብር ይገባቸዋልም ነው ያሉት ከንቲባዋ፡፡
ከሁሉም በላይ የመንገድ ፕሮጀክቶቹ በሚከናወኑባቸው አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች በወሰን ማስከበሩ ሂደት በከፍተኛ የልማት አጋርነትና የአገር ግንባታ ባለቤትነት ላሳዩት ትብብር ከንቲባዋ ምስጋና አቅርበዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

