Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

“የበቃ” ዘመቻ አካል የሆነ ሰላማዊ ሰልፍ በጣሊያን፣ ስፔን እና አውስትራሊያ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “የበቃ” ወይም ‘#NoMore‘ ዘመቻ አካል የሆነ ሰላማዊ ሰልፍ በጣሊያን ቱሪን፣ ስፔን ማድሪድ እና አውስትራሊያ አዴላይድ ከተማ ተካሄደ።
 
ሰልፉ በሁለቱ ከተሞች በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት ተካሂዷል።
 
በጣሊያን ቱሪን በተካሄደው ሰልፉ አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና ጫና የሚያወግዙ እንዲሁም ለሀገሪቱ ሉዓላዊነትና አንድነት መጠበቅ ያላቸውን ድጋፍ የሚገልጹ መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡
 
በተጨማሪም ሀገራቱ በኢትዮጵያ ላይ እያሳደሩ ያሉትን ኢኮኖሚያዊ ጫና እና በየሚዲያዎቻቸው የከፈቱትን የሃሰት ዘመቻ እንዲያቆሙ ጠይቀዋል፡፡
 
ሰልፈኞቹ አሸባሪው ህወሓት የፈጸመውን ጭፍጨፋና ያደረሰውን ጥፋት የሚያወግዝ እና የኢትዮጵያን መንግስት የሀገሪቱን ህልውና እና ሉዓላዊነት ለመጠበቅ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የሚደግፉ መልዕክቶችን ማሰማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በተመሳሳይ በስፔን ማድሪድ ሰልፈኞቹ “አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ አገራት ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት ማቆም አለባቸው” የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።
 
አሸባሪው ሕወሓት እየፈጸማቸው ያሉ ግፎችን ያወገዙት ሰልፈኞቹ ከኢትዮጵያ ጎን ነን እንዲሁም ኢትዮጵያ ታሸንፋለች የሚሉ መልዕክቶችን በማስተላለፍ አጋርነታቸውና ድጋፋቸውን መግለጻቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።
 
“የበቃ” ወይም ‘#NoMore‘ ዘመቻ አካል የሆነ ሰላማዊ ሰልፍ በሌላኛዋ የስፔን ከተማ ባርሴሎና የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ 2 ቀን 2014 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡
 
በደቡብ አውስትራሊያ አዴላይድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የ’#በቃ’ ‘#NoMore‘ ዘመቻ አካል የሆነ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።
 
ሰልፈኞቹ በመልዕክታቸው አሸባሪው ሕወሓትና ተላላኪዎቹ ያደረሱትን ዘረፋና ውድመት፣ አስገድዶ መድፈርና የሰላማዊ ሰዎች ጅምላ ግድያን አውግዘዋል።
 
ሰለባ ለሆኑ ወገኖችም በተለያየ መንገድ አጋርነታችን እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
 
አንዳንድ ምዕራባውያን ሃገራት በተለይም አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉ ያለውን ያልተገባ ጫና እንዲሁም የዜና አውታሮቻቸውም የሚያሰራጩትን አድሏዊና የተዛባ መረጃ እንዲያቆሙ ጠይቀዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version