አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ተቋማት በአሸባሪው ህወሓት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አስረከቡ፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ከ8 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የዓይነት ድጋፍ ማድረጉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በተጨማሪም በአሸባሪው ቡድን ጉዳት የደረሰባቸው የውሃ ተቋማት ተጠግነው ወደ አገልግሎት የሚገቡበት ሁኔታ እንደሚመቻች የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል የጋምቤላ ክልል በአፋር ክልል በአሸባሪው ህወሓት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የ3 ሚሊየን ብርና የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት፥ ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
በመላ አገሪቱ የሚገኙ ዜጎች የሚያደርጉት ድጋፍ ወንድማማችነትን የበለጠ የሚያጠናክር ነው፤ ለዚህም ምስጋና ይገባል ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ለአገር መከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ ሁልጊዜም ከሰራዊቱና ከተፈናቃይ ወገኖቻችን ጎን ነን ብለዋል።
በሌላ በኩል የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎትና ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሰራተኞች ደብረብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች የአይት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወልደ አማኑኤል÷ ለተደረጉ ድጋፎች ምስጋና አቅርበዋል።
በሳምራዊት የስጋት
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

