አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የአካባቢያቸውን ሠላም በንቃት የሚጠብቁ የተጠባባቂ ደጀን አባላት ተመረቁ፡፡
አባላቱ ”እኔ የአካባቢዬ ፖሊስና ዘብ ነኝ” በሚል መሪ ቃል ለ15 ቀናት የተሰጣቸውን መሠረታዊ ስልጠና በማጠናቀቅ ነው የተመረቁት፡፡
በቆይታቸውም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ መሳሪያ መፍታትና መግጠም እንዲሁም በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ወስደዋል።
የሐረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብዱጀባር መሐመድ፥ሰልጣኞች ሀገር ለማፍረስ ግልጽ ጦርነት በከፈተው አሸባሪው ህወሓት እና ጋላቢዎቹ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መሪነት አንጸባራቂ ድሎች እየተመዘገቡ ባለበት ወቅት መመረቃችሁ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
የአሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ የጥፋት ኃይሎች በህብረተሰብ ውስጥ ተሰግስገው ሊኖሩ ስለሚችሉ ይህ ተጠባባቂ ደጀን ሠራዊት የአካባቢውን ሠላምና ጸጥታ በማስጠበቅ የአሸባሪዎችን እኩይ አላማ ማክሸፍ እንደሚኖርበት አሳስበዋል፡፡
ተመራቂዎቹ በበኩላቸው የአካባቢያቸውን ሠላምና ጸጥታ የማስጠበቅ ስራ ከጀመሩ በኋላ በአካባቢያቸው የጸጥታ ስጋት መቀነሱን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው በመቀጠል የአሸባሪዎቹን ሴራ በማክሸፍ የአካባቢያቸው ጸጥታ አስተማማኝ እንዲሆን ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ነው ያረጋገጡት።
በተሾመ ኃይሉ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

