Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሸባሪው ህወሓት የደሴ ሪፈራል ሆስፒታልን ሙሉ ለሙሉ ዘርፏል፤ መውሰድ የማይችለውን አውድሟል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ ) የአሸባሪው ህወሃት ወራሪ ቡድን የደሴ ሪፈራል ሆስፒታልን ሙሉ ለሙሉ ከመዘርፉም በላይ መውሰድ የማይችለውን አውድሟል።
 
የሆስፒታሉ ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ ጌታቸው መታፈሪያ እንዳሉት÷አሸባሪ ቡድኑ ስብዓዊ አገልግሎትና ህይወት የማዳን ስራ እየሰራ ባለው የደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል።
 
አሸባሪ ቡድኑ ከሆስፒታሉ በተጨማሪ በወረራ ይዟቸው በነበሩ አካባቢዎች የመንግስትና የግለሰብ ንብረቶችን መዝረፉና መውሰድ ያልቻላቸውን ሙሉ በሙሉ ማውደሙ ተገልጿል።
 
የሽብር ቡድኑ በተለይ የህዝብ መገልገያ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ዘረፋና ውድመት የፈጸመ ሲሆን፤ ከእነዚህ ተቋማት መካከል የደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ተጠቃሽ ነው።
 
ጊዜያዊ አስተባባሪው ለኢዜአ እንደገለጹት የአሸባሪው ቡድን ወራሪ ሃይል፥ መድሃኒትን ጨምሮ ግዙፍ የህክምና ማሽነሪዎችን ዘርፎ ወስዷል።
 
በተለይ በቅርቡ ተመርቆ በሆስፒታሉ ውስጥ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረውን የኦክስጅን ማምረቻ ሙሉ ለሙሉ ተዘርፎ ተወስዷል ብለዋል።
 
አሸባሪ ቡድኑ በቅርቡ ተገዝተው አገልግሎት መስጠት የጀመሩ በሆስፒታሉን አልጋዎች ጭምር አውድሟቸዋ ነው ያሉት።
 
መውስድ ያልቻሏቸውን መድሃኒቶች ጥቅም እንዳይሰጡ አድርገው እንዳወደሟቸውም ጊዜያዊ አስተባባሪው ተናግረዋል።
 
አሸባሪ ቡድኑ የሆስፒታሉን ጀኔነተር ነዳጅ ዘርፎ በመውሰድና ሆስፒታሉ ነዳጅ እንዳያገኝ በመከልከል መትረፍ የሚችሉ ህመምተኞች እንዲሞቱ ማድረጉንም ነው የገለጹት።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version