አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “1 ሚሊየን ወደ ሃገር ቤት “ጥሪ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵውያ ወዳጆች መልካም ምላሽ እያሳዩ መሆኑን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ፡፡
የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ዛሬ በሰጡት መግለጫ “1 ሚሊየን ወደ ሃገር ቤት “ጥሪ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች መልካም ምላሽ እያሳዩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በጥሪው መሰረት ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት እንቅስቃሴ መጀመራቸውንና ይህን እንቅስቃሴ ለማገዝም የተለያዩ ተቋማት የተለያዩ ስራዎችን እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡
በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከትኬት ዋጋ 30 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን ጠቁመው፥ ሌሎች አገልግሎት ሰጪዎችም ቅነሳ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ነው ያሉት፡፡
ይህን የሚያስተባብር ግብረሃይል መቋቋሙንም ጠቅሰዋል፡፡
ይህ የአንድ ሚሊዮኖች ዘመቻ ታሪካዊ ጥሪ በመሆኑ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የሀገራቸውን ሰላም እንዲመሰክሩና መልካም ገጽታዋን እንዲገነቡ መልዕክት እናስተላልፋለን ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታው፡፡
በፌቨን ቢሻው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!