Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሶማሌ ክልል የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ሰላምና አንድነት ምክር ቤት በክልሉ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ምክር ቤቱ በክልሉ የተከሰተውን ድርቅ አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል፡፡

በመግለጫውም ÷ የክልሉ ህዝብ በተፈጥሮ ድርቅ አደጋ ምክንያት ከቀያቸዉ የተፈናቀሉ ወንድሞቻቸውን ባላቸዉ ነገር እንዲያግዙና በድርቅ የተጎዱ አቅመ ደካማ የሆኑትን የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲረዱ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም ዳያስፖራው ማህበረሰብ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው የተፈጥሮ ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች በሚደረገው ድጋፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ነው መልዕክት የተላለፈው፡፡

በተመሳሳይ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች በድርቅ የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች በሚደረገው ድጋፍ የበኩላቸዉን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረቡን ከሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version