Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፈረንሳዩ ጀኔራል ኤሌክትሪክ እና ከቻይናው ሲኖ ሃይድሮ ኩባንያዎች ጋር ብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል ለመገንባት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አሸብር ባልቻ፣ በምስራቅ አፍሪካ የጀኔራል ኤሌክትሪክ ንዑስ ቀጣና የሽያጭ ኃላፊ አቶ ማንያዘዋል ተስፋዬ እና የሲኖ-ሃይድሮ ተወካይ ቲያን ሆንግጁን ናቸው ስምምነቱን የተፈራረሙት፡፡
ስምምነቱ ሁለት ብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከላት ግንባታዎች የማከናወን እንዲሁም በሁሉም የኃይል ማመንጫ እና ማከፋፈያ ጣቢያዎች የመቆጣጠሪያና ለክትትል የሚረዱ ሥርዓቶችን የመዘርጋት ሥራዎችን ያጠቃልላል መባሉን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የፕሮጀክቱን ግንባታ ጀኔራል ኤሌክትሪክ እና ሲኖ ሃይድሮ ኩባንያዎች በጋራ የሚያካሒዱት ሲሆን÷ የማማከር ሥራውን ደግሞ የፊንላዱ ሒፋብ የተሰኘው ኩባንያ እንደሚያከናውነው በሥምምነቱ ላይ ተገልጿል፡፡
ፕሮጀክቱ በ3 ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ወደ ሥራ የሚገባ ሲሆን÷ ለዚህም ከ57 ነጥብ 67 ሚሊየን ዩሮ እና ከ102 ሚሊየን ብር በላይ በጀት ተይዞለታል፡፡
የፕሮጀክቱ የፋይናንስ ወጪ 1/3ኛው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቀሪው ደግሞ 2/3ኛው በፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version