አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሙስናን መዋጋት የዜጎች ሁሉ ኃላፊነት መሆኑን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡
ዘንድሮ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “በሥነ ምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና ለፀዳች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል ነው፡፡
ፕሬዚዳንቷ ቀኑን አስመልክተው በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንዳሉትም ፥ አመራሮች የፀረ ሙስና እቅዶችን በመንደፍና በማስፈጸም ከፍተኛ ሚና አላቸው፡፡
የፀረ ሙስና ትግል ሥነ ምግባራዊ አሠራር ባህል ለመፍጠር ነው ያሉት ፕሬዚዳንቷ፥ ሙስናና ብልሹ አሠራር ካለ ሠላም፣ መረጋጋት፣ ልማት፣ ጠንካራ የሥራ ባህል እንደማይኖሩ ገልጸዋል፡፡
አክለውም ሙስናን መዋጋት የዜጎች ሁሉ ኃላፊነት እንደሆነ አንስተዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

