አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ በቀጣይ ቀናት የታሪፍ መጠን ማሻሻያ እንደሚደረግ የትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።
በከተማዋ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ አሽከርካሪዎች አዲሱ የታሪፍ መጠን ይፋ ሳይሆን ምንም ዓይነት ዋጋ ባለመጨመር አገልግሎቱን በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ቢሮው አሳስቧል፡፡
የዓለም አቀፍ ነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ መደረጉ ይታወሳል፡፡
ይህንን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ ጥናቱን በማጠናቀቅ ላይ ሲሆን ፥ በቀጣይ ቀናት ይፋ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
የታሪፍ ማሻሻያው ተጠናቆ ይፋ እስኪሆን ቀደም ሲል በነበረው የታሪፍ ዋጋ አገልግሎቱ የሚሰጥ እንደሚሆን ቢሮው አስታውቋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

