Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኮምቦልቻና ደሴ ከተሞች ዛሬ የኤሌክትሪክ ሃይል እንዲያገኙ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮምቦልቻ እና ደሴ ከተሞች ዛሬ የኤሌክትሪክ ሃይል እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታወቀ፡፡
 
በሸዋ ሮቢት ኮምቦልቻ መስመር የተጎዳውን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የሚጠግነው ቡድን አባላት የኮምቦልቻና ደሴ ከተሞች ዛሬ ኤሌክትሪክ ማግኘት እንዲችሉ በርብርብ እየሰራ መሆኑ ተነግሯል፡፡
 
የጥገና ቡድኑ ትናንት ምሽት የጥገና ሂደቱን በየከተሞቹ የደረሰውን ጉዳትና የህብረተሰቡን ስሜት የተመለከተ አጠቃላይ ግምገማ አድርጓል፡፡
 
በዚህም የኮምቦልቻ እና ደሴ ከተሞች የኤሌክትሪክ ሃይል እንዲያገኙ ለማድረግ የቻለውን ያህል ጥረት እንደሚያደርግ ነው ቃል የገባው፡፡
 
የጥገና ቡድኑ ትናንት ከካራቆሬ-ከሜሴ ያለው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና አጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
 
የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ውቤ÷ የቴክኒክ ቡድኑ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከሸዋሮቢት እስከ ከሚሴ ያለውን መስመር ጠግኖ ለአገልግሎት ለማብቃት ያደረገውን ጥረት አድንቀዋል፡፡
 
ከባድ መስዋዕትነት በመክፈል የህዝቡን ችግር ለመፍታት ያደረጋችሁትን ርብርብ ተቋማችንና ህብረተሰቡ ሁሌም ሲያስታውሰው ይኖራል ማለታቸውንም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version