አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሂዩማን ራይት ዎች የህወሓት የሽብር ቡድን በወረራ ይዟቸው በነበረው የአማራ ክልል ጭና እና ቆቦ ከተሞች ንፁሃን ዜጎችን በጅምላ መጨፍጨፉን ገለፀ፡፡
ድርጅቱ ትናንት ባወጣው ሪፖርት እንዳለው፥ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ከፈረንጆቹ ነሐሴ 31 እስከ መስከረም 9 ቀን 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ በአማራ ክልል በያዛቸው አካባቢዎች በርካታ ንፁሃን ዜጎችን በጅምላ ገድሏል፡፡
ከዚህም ውስጥ የጭና ቀበሌ አንዱ ሲሆን፥ የአካባቢው ነዋሪዎች ለድርጅቱ እንደነገሩት የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች 26 ሰላማዊ ዜጎችን በገፍ ገድለዋል፡፡
በቆቦ ከተማም እንዲሁ መስከረም 9 የህወሃት ታጣቂዎች በአራት የተለያዩ አጋጣሚዎች 23 ሰዎችን መግደላቸውን የዓይን እማኞች ተናግረዋል ነው ያለው ሪፖርቱ።
የድርጅቱ የግጭት ዳይሬክተር ላማ ፋኪህ “የህወሃት ታጣቂዎች ለሰው ልጅ ህይወት እና ለጦርነት ህግጋት ያላቸውን ግድየለሽነትና ጭካኔ በእጃቸው ስር ያሉትን (በእስር የያዟቸውን) ሰዎች በመግደል አሳይተዋል ነው ያሉት።
እነዚህ ግድያዎችም በአማራ ክልሎች ተፈጽመዋል የተባሉ የጦር ወንጀሎችን በገለልተኛ አካል ማጣራት እንደሚያስፈልግ ያመላክታሉ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ።
በሌላ በኩል ጦርነቱ ወደ አጎራባች የአማራ ክልል መስፋፋቱ ከፍተኛ መፈናቀል አስከትሏል ያለው ሪፖርቱ፥ በክልሉ 3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲልም አመላክቷል፡፡
ድርጅቱ የሽብርተኛው የህወሃት ታጣቂዎች አለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግን በማክበር በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በአስቸኳይ ማቆም አለባቸው ሲልም አሳስቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

