Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

እስራኤል የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት ለማልማትና ለማበልጸግ የበኩሏን ሚና እንደምትወጣ አረጋገጠች

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል በውሃ፣ በመስኖና በግብርና ቴክኖሎጂዎች ያላትን ልምድ በማካፈልና በማልማት ለኢትዮጵያ ዕድገት የበኩላችንን ሚና እንወጣለን ሲሉ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ አረጋገጡ፡፡

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።

በውይይቱም በመስኖ ቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይል ልማትና በኢንቨስትመንት ዙሪያ መክረዋል፡፡

ኢንጂር አይሻ መሐመድ÷ “የእስራኤል ባለ ሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በመስኖ ልማት ዘርፍ የሚሰማሩ ከሆነ ምቹ ሁኔታዎችን እንፈጥራለን” ብለዋል ፡፡

በተጨማሪም በሰው ሃብት ልማትና የመስኖ ቴክኖሎጂ እስራኤል ድጋፍ እንዲታደርግ እንፈልጋለን ብለዋል ፡፡

የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ በበኩላቸው ÷ “ኢትዮጵያና እስራኤል ረዥም የታሪክና የባህል ትስስርና ቁርኝት እንዳላቸው ገልጸው፥ በእስራኤል ያሉ የውኃ፣ የመስኖና የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣትና ልምድ በማካፈል በሀገሪቱ በዘርፉ ያለውን የተፈጥሮ ሀብት በማልማት ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካም ዕድገት የበኩላችንን ሚና እንወጣለን” ብለዋል፡፡

እስራኤል በውሃ ምርምርና ቁፋሮ ታወቂ ሀገር መሆኗን የገለጹት አምባሳደሩ ኢትዮጵያ በገጸ-ምድርና በከርሰ ምድር ውኃ ሀብት የበለጸገች በመሆኗ በመስኖ ልማት ዘርፍ እስራኤል ለኢትዮጵያ ድጋፍና ኢንቨስት ለማድረግ ዝግጁ ናት ማለታቸውን ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version