Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያውያንን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት የሚያሸንፍ ምድራዊ ሃይል የለም-የአጋሮ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተምሳሌትነት ለሀገር የሚከፈል የትኛውንምን ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ነን ሲሉ የአጋሮ ከተማ እና አካባቢ ነዋሪዎች ገለጹ።
ነዋሪዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የመጀመሪያውን ምእራፍ አጠናቀው ወደ መደበኛ ቢሯቸው በመመለሳቸው የተሰማቸውን ደስታ በሰልፍ ገልጸዋል።
 
ነዋሪዎቹ ጠላት እስኪጠፋ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለሀገር የሚከፈልን የትኛውንምን ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ነው የገለጹት።
 
የአጋሮ ከተማ ከንቲባ አቶ ነዚፍ መሐመድአሚን፥ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ፈለግ በመከተል አሸባሪው ህወሓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስኪደመሰስ በሁሉም ግንባሮች ለሀገር መቆም ያሻል ብለዋል፡፡
 
ከንቲባው የአጋሮ ከተማ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት 8 ሚሊየን ብር መለገሱን እና አሁንም ለሰራዊቱ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
 
የጅማ ዞን የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ነጃት ከድር በሽብር ቡድኑ ላይ የተገኘውን ድል በልማትም መድገም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
 
አሸባሪው ቡድን በአማራ እና አፋር ክልል ያደረሰው ሰብዓዊ በደል እና ቁሳዊ ውድመት ለመጠገን ከህዝባችን ጎን ሆነን መልሶ ማቋቋም ይጠበቅብናልም ነው ያሉት።
 
በወርቅአፈራው ያለው
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version