አዲስ አበባ፣ታህሳስ 1፣2014 (ኤፍ ቢሲ) አሜሪካ ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲ ያጣችበት ሁነት ከኢራን ቀጥሎ ትልቁ የስትራቴጂክ ውድቀት መሆኑን የካዉንተር ፓንች መፅሄት አምደኛ ቶማስ ማዉንቴን ገለጸ።
ተንታኙ በፅሁፋቸው የአሜሪካ መንግሥት የሚወግንለት አሸባሪው ህወሓት በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የኢትዮጵያ መንግሥት ለማስወገድ ያደረገው ሙከራ መክሸፉን ተከትሎ አሜሪካ ስልታዊ አጋሯን ኢትዮጵያን የማጣት እውነታን መጋፈጧን አስነብበዋል።
የአሁኑ የዋሽንግተን ስህተት በፈረንጆቹ 1979 ኢራን ላይ ከፈፀመችው ቀጥሎ ትልቁ መሆኑንም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ጥምር ጦር አሸባሪው ህወሓት በወረራ ይዟቸው የነበሩ ቦታዎችን በ10 ቀናት ውስጥ ነጻ ማውጣቱንም በጽሁፋቸው አንስተዋል።
ከዚህ ባለፈም የአሸባሪው ቡድን አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያቀረቡትን የእጅ ስጡ ጥሪ ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩት የሽብር ቡድኑ አባላት እጃቸውን መስጠታቸውን ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት እንዳመላከተውም ሀገሪቱ ከዚህ በኋላ ከአሜሪካ መራሹ የምዕራባውያን ኒዮኮሎኒያሊዝም እሳቤ በተቃኘው ግንኙነት መቀጠል እንደማትፈልግ ግልፅ አድርጋለችም ነው ያሉት።
ይባስ ብሎ በጂቡቲ የአሜሪካ ጦር አዛዥ ዋሺንግተን በኢትዮጵያ ለሚፈፀም ወታደራዊ ተልዕኮ መዘጋጀቷን መግለጻቸው፥ ኢትዮጵያን ወታደራዊ አማራጮችን እንድትመለከት አስገድዷታል ሲሉም ነው በጽሁፋቸው ያነሱት። ይህን ተከትሎም ከቻይና ጋር ጠንካራ የፖለቲካና የምጣኔ ሃብት ትስስር እየፈጠረች መምጣቷን አንስተዋል።
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ በፈፀመችው ስህተት ራሷን በጥይት ተኩሳ እንደገደለች እቆጥረዋለሁ የሚሉት ፀሀፊው፥ ዋሽንግተን ኢትዮጵያን በማጣቷ አሜሪካ በአፍሪካ ህዝቦች ዘንድ ሃያልነቷን ታጣለች ባይ ናቸው።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

